ለክርስቲያን - ለመጋቢዎች | (በ ቸክ ላውለስ ከተጻፈው ጽሁፍ ተሸሽሎ የቀረበ)

መጋቢዎች ፍጹማን ናቸው ብዬ አላምንም ፡፡ እኛ መጋቢዎች ጥፋት እናጠፋለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግትሮች እና ግድ የለሾች እንሆናለን፡፡ በዚያው ጊዜ ደግሞ አብዛኞቹ የማውቃቸው መጋቢዎች እግዚአብሔርን የሚወዱ እና በቅን ልብ ጌታን የሚከተሉ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኖቻቸውን እና ምዕመኑን የሚወዱ እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ታዲያ የመጋቢነት ጥሪ በውስጡ ብዙ ልብን የሚያሳምሙ ጉዳዮች የሚሰሙበት እና የሚታዩበት እንደሆነ ተምረዋል፡፡ በአገልግሎት ዘመን የመጋቢዎችን ልብ የሚያሳምሙ አስር ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. የቤ/ክ አባላት ትዳር ሲበትን -

ከሁለቱም የትዳር አጋሮች የሚመጡትን አቤቱታዎች መጋቢዎች የማድመጥ ግዴታ አለብን፡፡ ፍቺ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በቤተሰብ ላይ የሚያደርሰውን መዘዝ እናውቀዋልን፡፡ ስሊዚህም በሚፋቱ ምዕመኖቻን እጅግ ልባችን ይሰበራል፡፡

  1. ወጣት አባላቶች በሕይወታቸው ወደ አደጋ የሚወስዳቸውን ውሳ ሲወስኑ ማየት፡-

ማናችንም ቢሆን የምናገለግላቸው ወጣቶች የተሳሳተ ውሳኔን ሲወስኑ እና በውሳያቸው ደግሞ ሎወጡት የማይችሉት ችግር ውስጥ ሲወድቁ ማየት አንሻም፡፡ ይበልጥ የሚሳዝነን ደግሞ እኛ ልናስቆማቸው አለመቻላችን ነው፡፡ አንዳንድ ወጣቶች የተሳሳ ትዳር ውስጥ ለመግባት ሲወስኑ አልያም ወጣት ሴቶች ከትዳር በፊት ጸነሰው ሲገኙ አልያም ወጣች ትምህርታቸውን ያለ በቂ ምነክንያት ሲያቆሙ ማየት ለእኛ ለመጋቢዎች ትልቅ ሕመም ነው፡፡

  1. ስብከቶቻችን እንዳሰብነው ጠንካራ ሳይሆኑ ሲቀሩ

አብዛኛውን ጊዜ የመጋቢዎች ወቃሾች ራሳው መጋቢዊች ናቸው፡፡ አንዳንዶቻችን ከሰበክን በኋላ ‹‹አሻሽዬ ብሰብክ ኖሮ›› ብለን ለቀናት በቁጭት እናስባለን፡፡ ስለዚህም ጥሩ ያልሰበክን ሲመስለን ራሳችንን እንወቅሳለን፡፡

  1. ሌሎች በሰሩት ሐጢአት እኛ ከእነሱ በላይ እናዝናለን

አንዳንድ አባላቶቻችንን ‹ንስሃ ግቡ! ተመለሱ!› ብንላቸውም እንደማይመለሱ እናውቃለን ፡፡ በስህተታው በቀጠሉ ቁጥር ለእኛ ትልቅ የለብ ስብራት ነው፡፡

  1. በቤ/ክ የስነስርዓት እርምጃ በአባላቶቿ ላይ ስትወስድ

በአገልግሎት ዘመኔ ሁሉ በምክር አልመለስ ያሉ አባላቶችን ከቤ/ክ እንደማሰናበት የሚያም ነገር አላውቅም፡፡ ምንም እንኳን ስነስርዓት ማስያዙ ትክክል ቢሆንም በመጋቢነቴ ልረዳቸው ባለመቻሌ እጅግ በጣም እንዳዝን ያደርገኛል፡፡ አብዛኞቹን ደግሞ ስለጸልይላቸው ስለምቆይ በእነርሱ መለየት እጅግ እጎዳለሁ፡፡

  1. የምንመራት ቤተ ክርስቲያን ሳታድግ ስትቀር

እኛ መጋቢዎች አብዛኛውን ጊዜ ቁጥር ጉዳይ እጅግ ያስጨንቀናል፡፡ አንዳዴም የምዕመናን ቁጥር ጣኦት ሊሆንብን ይቻላል፡፡ አብዛኘውን ጊዜ ግን ከቅን ልብ በመነጨ እና ብዙዎችን ለመድረስ ካለ ጉጉት የተነሳ ብዙ መጋቢዎች የቤ/ክ አባሎቻቸው በቁጥር እንዲበዙላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር ታዲያ የብዙ መጋቢዮች ልብ ይሰበራል፡፡

  1. የቤተሰቦቻችንን ብቸኝነት ስናይ

እዚህ ጋር ማንም ላይ መፍረድ አልፈልግም፡፡ ነገር ግን ግልጽ ሊሆን የሚገባው የመጋቢው ቤተሰቦች ከሌሎች አባላት ይልቅ ጫና እንዳለባቸው ነው፡፡ በመጋቢው አድካሚ እና ጊዜን የሚወስዱ ስራዎች ምክንያት ቤተሰቡ ብቸኝነት ይሰማቸዋል፡፡ ይህንን ማየት ደግሞ ለመጋቢው ያሳምማል፡፡

  1. ጌታን ያላመነ ሰው ቀብር እጅግ በጣም ያሳዝነናል፡፡

በቀብሮች ላይ እንድንናገር ወይንም ጸሎት እንድንመራ እንጋበዛለን፡፡ ታዲያ ጌታን ሳያውቅ የሞተ ሰውን ቀብር መምራት ለእኛ እጅግ ትልቅ የልብ ሕመም ነው፡፡ ለቅሶውን በአደባባይ ባናለቅስም በልባችን ግን እጅግ ባጣም እናዝናን፡፡

  1. ከአባላቶቻችን ጋር መግባባት ሲያቅተን እና ጓደኞች ልናደርጋቸው ሳንችል ስንቀር

አብዛዛኛውን ጊዜ ይህ የአባላቶቻችን ችግር ሳይሆን የእኛ የመጋቢያን ችግር ነው፡፡ መግባባት ይከብደናል፡፡ መተዋወቅ ያቅተናል፡፡ ሌሎችን ማቅረብ እንቸገራለን፡፡ ከዚህም የተነሳ ለብቸኝነት እንጋለጣለን፡፡ ይህ ደግሞ ልባንን ያሳምመዋል፡፡

  1. እነዚህን ሃሳቦች ስንገልጥ የጥፋኝነት ስሜት ይሰማናል፡፡

ምናልባት ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶችን የማስተናግደው እኔ ብቻ ልሆን እችላለሁ፡፡ እኛ መጋቢዎች ስሜቶቻችንን መግለጽ በራሱ ሌላ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን ያደርገናል፡፡ ስለዚህም በመጋቢዎች ስም እንዲጸለይልን እጠይቃለሁ፡፡

በዚህ ሳምንት ለመጋቢዎችችሁ ጸሎት አድርጉ!

Comments powered by CComment