Articles - Newsflash

A A A

ለክርስቲያን ዜና (በምስጋና ሙሉነህ) ፤ ጥቅምት 24 ፤ 2011 ዓ.ም 

በፓኪስታኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባት ለስምንት ዓመት ያህል በቁጥጥር ስር የነበረችው አንዲት ክርስቲያን ሴት በነጻ ተለቃለች። የፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ሳኩብ ኒዝመር የፍርድ ውሳኔውን ካነበቡ በኋላ ቢቢ በምላሹ : - ‹‹እኔ የምሰማውን ማመን አልችልም! አሁን ልወጣ እችላለሁ? በእርግጥ ይለቁኛል?›› በማለት በስልክ ደስታዋን በሲቃ ገልጻለች።  ቢቢ እ.ኤ.አ በ2009 ነብዩን መሃመድን ተሳድባለች በሚል ተከሳ የሞት ፍርድ ተፈርዶባት ለ8 ዓመታት ለብቻዋ ታስራ ነበር፡፡

የ5 ልጆች እናት የሆነችው ዔሺያ ቢቢ አዝመራ ሰብሳቢ ሆና በምትሰራበት ቦታ ላይ ነበር ለክሷ ምክኒያት የሆነው ክስተት የተፈጠረው። ሲ.ዔን.ዔን(CNN) እንደዘገበው ቢቢ ከውሃ ጉድጉድ ውሃ እንድታመጣ ትጠየቃለች።  ሙስሊም የስራ ባልደረቦቹዋም እሷ ከቀዳችበት ባልዲ ውሃ አንጠጣም በማለት ይቃወማሉ።  ምክንያታቸውም እሷ ክርስቲያን ስለሆነች የውሃውን መቅጃ በመንካት አርክሳዋለች የሚል ነበር።  ነገሩ ነብዩ መሃመድን ሰድባለች ወደሚል ማስረጃ ወደሌለው ሙግት አመራ፤ ጉዳዩም ሙስሊም የሃይማኖት አባቶች ጋር ደረሰ።  ፍርድ ቤትም በቢቢ ላይ ክስ መስርቶ በ 2010 ሞት ፈረደባት።  የመጀመርያው ደረጃ ፍርድ ቤቶች በ 2015 ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመሰማት እስኪስማሙ ድረስ የመጀመሪያዎቹን የይግባኝ ጥያቄዎች ውድቅ አደረጉ። በወቅቱም የማይወዷት ሴቶች እሷን ለመበቀል ያደረጉት ተንኮል እንደነበር ቢቢ ተናግራለች። 

የፓኪስታን የአስነዋሪ ስድብ ደንቦች አሁንም ውዝግብ እያስነሱ ነው።  የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም እያወገዙት ይገኛሉ።

በፓኪስታን ውስጥ ህጎችን በተመለከተ ውስጣዊ ግጭቶች አሉ። ተህሪክ ለባይክ(TLP) የተባለው እስላማዊ ቡድን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቢቢን በነጻ ቢለቅ በአገሪቱ ጎዳናዎች በመውጣት እንደሚቃወም አሳውቆ ነበር።  ስለዚህም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በተለያዩ የፓኪስታን ከተሞች ብዙው ህዝብ ለተቃውሞ በመውጣት ከፖሊሶች ጋርም ግብግብ ፈጥሯል።  በፓኪስታን ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች በቢቢ ነፃ መውጣጥ በእጅጉ የተደሰቱ ቢሆኑም በሌላ ጎን ደግሞ የበቀል ጥቅት እንዳይደርስባቸው ይፈራሉ።  አንድ ክርስቲያን ሰው የፍርድ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ ከሰማ በኋላ "ለፓኪስታን ጸልዩ፣ ሁኔታው በግልጽ እየታየ ነው፣ እኔ በሥራዬ ላይ ነኝ እና የአካባቢው ጸጥታ አስከባሪዎች ለመጠበቅ መጥተዋል። እባካችሁ የእግዚአብሔርን ምሕረትንና ጥበብን እንዲሁም እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ አንድ አስደናቂ ሥራ እንዲያከናውን ጸልዩ።" ማለቱን ኦፕን ዶርስ (Open Doors) ተናግሯል።

በዓለም ዙርያ ለሚሰደዱ ክርስቲያኖች መብት ጥብቅና በመቆም የሚታወቀው የኦፕን ዶርስ ድርጅት በቢቢ መለቀቅ የተሰማውን ደስታ በቃል አቀባዩ በኩል "የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእስያ ክር ላይ በሀሰት ውንጀላዎች ላይ የተመሰረቱትን የእስያ ቢቢን ክስ እንደጣለ በማወቃችን እፎይታ እናገኛለን።  ይህ ውሳኔ ፓኪስታን በአገሪቱ ውስጥ የሃይማኖትና የሰብአዊ መብትን ለማስፋት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ተስፋ ሰጥቶናል" በማለት ገልጿል።

የቢቢ ባል አዚቅ ማሲህ "በጣም ደስተኞች ነን፤ ይህ አስደናቂ ዜና ነው። የእኛን እና በእነዚህ ሁሉ የስቃይና የመከራ ዓመታት አብረውን ሲጸልዩ የነበሩ ጸሎት የሰማውን እግዚአብሄርን እጅግ በጣም እናመሰግነዋለን" በማለት በሚስቱ ነጻ መውጣት ደስታውን ገልጿል። 

በአሁኑ ጊዜ በርካታ የምዕራባውያን አገራት ቢቢን እና ቤተሰቦቿን ተቀብለው ለማኖር ያላቸውን ፍላጎት እያሳዩ መሁኑን ዘገባዎች ያሳያሉ።

 

Pin It

Comments powered by CComment